አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

አዳዲስ ዜናዎች

 • የዲቪ ሎተሪ ምዝገባ ሊጀመር ነው

  በዚህ ዓመት ዲቪ ላይኖር ይችላል የሚል ስጋት የነበረ ቢሆንም የአሜሪካ ኤምባሲ እ.አ.አ. የ2019 የዲቪ ምዝገባ እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 3 ቀን 2017 እንደሚጀመር አስታወቀ፡፡ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስደትና በስደተኞች ላይ ባላቸው አቋም የተነሳ በዚህ ዓመት ዲቪ ላይኖር ይችላል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ ነበር፡፡

 • ለአዳዲስ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ 20 ቢሊዮን ብር በጀት ተያዘ

  በገንዘብ እጥረት ምክንያት በ2009 በጀት ዓመት አዳዲስ የጋራ መኖርያ ቤቶች ግንባታዎች ባይጀመሩም፣ በ2010 በጀት ዓመት በ20/80 እና በ40/60 ቤቶች ፕሮግራም ለ25 ሺሕ የጋራ ቤቶች ግንባታ 20 ቢሊዮን ብር በጀት ተያዘ፡፡

 • በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት የሰላም ኮንፈረንስ ሊካሄድ ነው

  በቅርቡ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ደም አፋሳሽ ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት፣ የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ ሊካሄድ ነው፡፡ ኮንፈረንሱን ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡

 • የሞያሌ ድንበርን ማለፍ ያልቻለው የኤክስፖርት ስኳር ውዝግብ አስነሳ
  • የኬንያ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ተጠይቋል
  • መፍትሔ ካልተገኘ ስኳሩ ወደ ወንጂ ሊመለስ ይችላል

  ከአንድ ወር በፊት ወደ ኬንያ ኤክስፖርት ተደረገ የተባለው ስኳር የኢትዮጵያ ሞያሌ ድንበርን አለማለፉን፣ የስኳር ምርቱን የገዛው መቀመጫውን በዱባይ ያደረገው ኩባንያ ችግሩን መፍታት አለመቻሉን ሪፖርተር ያገኛቸው መረጃዎች አመለከቱ፡፡

 • የመንገዶች ባለሥልጣን ኃላፊዎች ከሁለት ደረጃ አንድ ሥራ ተቋራጮች ጋር ክስ ተመሠረተባቸው
  • ለሁለቱም ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ያላግባብ ክፍያ መፈጸሙ ተገልጿል
  • ሳትኮንና ሀዚ አይአይ ሥራ ተቋራጮች በክሱ ተካተዋል

  ከሐምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ ሲካሄድባቸው በከረሙት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሰባት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ በገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገምሹ በየነ (በሌሉበት) እና በዲኤምሲ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል ማሞ (በሌሉበት) ላይ ዓርብ መስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡

 • ፍርድ ቤት ለዓቃቢያነ ሕግ የመጨረሻ የተግሳጽ ቅጣት ሰጠ
  • በገንዘብ ሚኒስቴርና በስኳር ኮርፖሬሽን ተጠርጣሪዎች ላይ የመጨረሻ ቀጠሮ ተሰጠ

  የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት፣ ዓርብ መስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በሙስና ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዓቃቢያነ ሕግ ላይ የመጨረሻ የተግሳጽ ቅጣት ሰጠ፡፡

 • መደማመጥ ቢኖር የት ይደረስ ነበር!

   ለመደማመጥ ሰከን ብሎ መነጋገር ያስፈልጋል፡፡ ስክነትና ትዕግሥት በሌለበት ከመጯጯህ የዘለለ ቁም ነገር አይገኝም፡፡ አስተሳሰቤ ተሸናፊ ይሆንብኛል ወይም በዓይኔ እንኳ ማየት የማልፈልገው ሰው ሊሞግተኝ ይችላል ተብሎ ከውይይት መሸሽ ተቀባይነት የለውም፡፡ በግለሰብ ደረጃም ሆነ በመንግሥት የዕለት ተዕለት ሥራ፣ በፓርቲ ፖለቲካም ሆነ በተለያዩ ጉዳዮች መነጋገር ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፡፡

 • በሰከነ አዕምሮ ለችግሮቻችን መፍትሔ እንፈልግ!

  የሰው ልጅ እርስ በርሱ በሚያደርገው ግንኙነት በሰከነ መንገድ መነጋገር፣ መወያየትና ብሎም መደራደር ትልቅ ጥቅም ያስገኝለታል፡፡ 

 • ሕዝብን እያጋጩ አገርን ማተራመስ በታሪክ ያስጠይቃል!

  አገርን ከቀውስ ወደ ቀውስ በማሸጋገር ትርምስ መፍጠር አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ በዜጎች ውድ ሕይወት ላይ መቆመር ያሳዝናል፡፡ የኢትዮጵያዊነት የጋራ መገለጫ የሆኑት ጨዋነት፣ አስተዋይነትና አርቆ አሳቢነት ወደ ጎን እየተገፉ ግንፍልተኝነትና ግትርነት እየገነኑ ነው፡፡ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ደም አፋሳሽ ግጭት በተቻለ መጠን በፍጥነት ካልቆመ፣ ሕዝብን ለዕልቂት አገርን ደግሞ ለማያባራ ጦርነት ይዳርጋል፡፡

 • ከሕዝብ ፈቃድ ውጪ መሆን ለማንም አያዋጣም!

  የአዲሱን ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ/አደረሰን የምኞት መግለጫ በመለዋወጥ፣ በዓሉ በተጠናቀቀ ማግሥት በቀጥታ ወደ አንገብጋቢው የአገር ጉዳይ መመለስ ተገቢ ነው፡፡

 • የከፍታው ዘመን ዕውን መሆን የሚችለው በኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴቶች ላይ ብቻ ነው!

  በአዲሱ ዓመት ከፀብና ከጥላቻ የፀዳች ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር ማለት አለብን፡፡ ይህ የመልካም ምኞት መግለጫ አገራቸውን የሚወዱ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ይሆን ዘንድ በብሩህ ተስፋ መነጋገር ይገባል፡

 • አዲሱን ዓመት በአዲስ ተስፋ እንቀበለው!

  አዲስ ዓመት ሲመጣ ሁሌም በተስፋ የመቀበል ፅኑ ፍላጎት አለ፡፡ አሮጌው ዓመት ተሸኝቶ አዲሱ ሲጠባ ሁሌም መንፈስን ማነቃቃትና ጥሩ ጥሩ ነገሮች መመኘት የተለመደ ነው፡፡ 

የ ሳምንቱ ዜና በ ምስለ ቀረጻ

ክቡር ሚንስተር

ማህበራዊ

ምን እየሰሩ ነው?